የማለዳ ወግ . . . አፋጣኝ ትኩረት የሚሻ የተፈናቃይ የኮንትራት ሰራተኞች ጥሪ . . .

ነቢዩ ሲራክ: ECADF አሮጌው የፈረንጆች አመት አልፎ በአዲስ አመት ከመግባቱ አስቀድሞ በዋዜማው ያየን የሰማነው በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩት የኮንትራት ሰራተኞች ውሎ አዳር ደስ አይልም ፡፡ በያዝነው ወርማ በተለያዩ የሳውዲ ጋዜጦች ሳይቀር የተዘመተብን ይመስላል ፡፡ የኮንትራት ሰራተኞች ተከላካይ ጠበቃ አጥተው ፤ በአሰሪዎች ሲባረሩ ፤ ሲደፈሩና አደጋው በርታ ሲል ተፍተው በኢንባሲና በቆንስል መስሪያ ቤቶች ጥገኝነት ይጠይቃሉ፡፡...